ኑና እንዋቀስ
ሕይወት ትሠምር ዘንድ፣ሰው ከአምላኩ ምሪትን፣ኃይልን፣ምክርን ወዘተ ሊቀበል ይገባዋል፡፡አለበለዚያ ሕይወት መደዴ ይሆናል፤ፍሬ
አልባም፡፡መኪና ወደ ጋራዥ ለእድሳት እንደሚወሰድ ሁሉ፣ወደ ጸጋ ዙፋኑ በመምጣት ምሕረቱንና ጸጋውን ልንቀበል ያስፈልገናል፤አንዴ
ብቻ ሳይሆን ሳናቋርጥ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል “ውኃውንም ከመድኃኒት
ምንጮች በደስታ
ትቀዳላችሁ”(ኢሳይያስ 12:3) የሚለውም ለዚህ ነው፤ወደ ምንጩ መጥተን የመቅዳቱ ኀላፊነት የኛ
እንደ ሆነ ሲያመለክት፣ያለ ማቋረጥ መሆኑንም፡፡
ሰው
ወደ ጌታው ሕልውና ሲመጣ፣ራሱን የማየት ጊዜ ያገኛል፡፡በሕይወቱ ያላስተዋላቸውን መሠረታዊ ችግሮች የመረዳትና የመገንዘብም ዕድል
ይኖረዋል፡፡ቃሉ “የተሰወረውን
ኃጢአታችንን በፊትህ ብርሃን፥
በደላችንንም በፊትህ አስቀመጥህ” (መዝሙር 90፡8) እንደሚል፣ ከሕሊናችን የተሰወሩና
ያልተናዘዝናቸው ኃጢአቶችን(እንዳሉም ያላሰብናቸውን) የማየት አጋጣሚው ይኖረናል፡፡
በጌታ
ፊት የምንሆንባቸው ጊዜያት የባከኑ እንደ ሆኑ ልናስብ አይገባም፤እንዳውም ጥሩ የሕክምና ጊዜ፣ጥሩ የመሠሪያ ጊዜ እንደ ሆነ እንጂ፡፡ታዲያ
በትሕትና የውስጣችንን ችግሮች ዘክዝከን፣ነፍሳችን አፍስሰን፣ከምር በሚፈስ እንባ ጥልቅ ንስሐዎችን ብንገባ፣የሚመጣው መታደስ ቀላል
አይሆንም፡፡እንዲህ ዓይነት ጊዜዎች ሲበዙልን ነው፣ለውጣችን የሚበዛው፤እድገታችንም ብዥታ የማይኖረው፡፡
ራሳችንን
ለመመርመር ጊዜያትን ማመቻቸት አስተዋይነት ይመስለኛል፡፡ጨክኖ ግላዊ ፍተሻ(personal inventory) ማድረግና ከጌታ ጋር
ለመሄድ መስማማት ጥበብ ሲሆን፣ወደ ፈጣሪ ሕልውና እየመጣ “ኑና እንዋቀስ”
(ኢሳይያስ 1፡18) በሚለው መንፈሳዊ መርሕ ያልተጎበኘ ሕይወት ችግር አለው፡፡ቃሉ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፣በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል”(ኢሳይያስ 30፡15) ይላልና፡፡
አዎ! የጸጥታ ጊዜ፣የእረፍት ጊዜ፣የመመለስና የንስሐ ጊዜያት ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ያኔ ኃይላችን ይታደሳል፣መንፈሳችን ይጠነክራል፡፡ያኔ በአዲስ አተያይና ምልከታ፣ተግዳሮቶቻችን እንገጥማለን፡፡መታከትም ይወገዳል፡፡በታደሰ ሕይወትም የሚሠራው ሥራም ብዙ ፍሬን ያፈራል፡፡……..
አዎ! የጸጥታ ጊዜ፣የእረፍት ጊዜ፣የመመለስና የንስሐ ጊዜያት ለሕይወታችን እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ያኔ ኃይላችን ይታደሳል፣መንፈሳችን ይጠነክራል፡፡ያኔ በአዲስ አተያይና ምልከታ፣ተግዳሮቶቻችን እንገጥማለን፡፡መታከትም ይወገዳል፡፡በታደሰ ሕይወትም የሚሠራው ሥራም ብዙ ፍሬን ያፈራል፡፡……..
No comments:
Post a Comment