Wednesday 31,2014
ከዕንቁ የሚበልጥ
ዋጋ
በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ሕይወትን የሚለውጥ ውድ ሕይወት ተገልጦልን ዕድለኞች ሆነናል፡፡ስለዚህም ይህንን ሕይወት ለሌሎች
ማካፈልን፣ከዕንቁ እንደሚበልጥ ዋጋ እናየዋለን፡፡
ኮሌጅ በነበርኩበት ጊዜ በምሣ ግብዣችን ላይ ትልቅ ሽልማት ስቀበል ንግግር አድርጌ ነበር፡፡የዚያን ቀን ለክርስቶስ ያለኝን
ፍቅር በሚገርም ሁኔታ ተረክሁ፡፡ንግግሬን ስጨርስ ከታዳሚዎች መሐል አንድ ሰው ወዳለሁበት መጥቶ “ልትረዳት የምትችል አንድ ሴት ሆስፒታል ውስጥ አለች፤አንተ የምትለውን
ልትሰማ ትፈልጋለች ” አለኝ፡፡በዚያን ጊዜ ፓስተር አልነበርሁም፡፡የምክክር አገልግሎት ዕውቀትና ክህሎት አልነበረኝም፤ቢሆንም
ለሰውየው ፈቃደኝነቴን ገለጽሁለት፡፡
ወዲያው ወደ ሆስፒታሉ አመራሁና፣ያች የ17 ዓመት ቆንጆ ልጅ አልጋዋ ላይ ሆና አገኘሁ፡፡የወንድ ጓደኛዋ ሳታስበው አንገቷ ላይ በሽጉጥ ተኩሶበት፣ከወገቧ
በታች መንቀሳቀስ አትችልም ነበር፡፡በአልጋው ላይ በሙሉ ሰውነቷ ቀጥ ብላ ተጋድማ ነበር፡፡ራሴን አስተዋውቄያት፣ሰው እንድጐበኛት
እንደጋበዘኝ ነገርኳት፡፡ከዚያም ፈራ እያልኩ “ያለሽበትን ነገር መረዳት
ይከብዳል” አልኳት፡፡ወዲያው ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፏ አፈትልኮ የወጣው ንግግር “ብችል ኖሮ ራሴን አጠፋ ነበር፣የምኖርበት ምክንያት የለኝምና” የሚል ነበር፡፡
የማደርገውን ነገር
ባጣ፣ወንጌሉን እንደ ወረደ በፊቷ ማቅረቤን ተያያዝኩት፡፡“አካልሽ ላይ
የሆነው አይደለም የሚያሳስበው፣ዘላለማዊ የሆነችው ነፍስሽ ላይ ሊሆን ያለው ነው እንጂ” አልኳት፡፡ “ስትሞቺ
አንድ ቦታ ለዘላለም ሕያው ሆነሽ ትኖሪያለሽ” ብዬ ቀጠልሁ፡፡ ከዚያም የበለጠ ደፈር በማለት “አየሽ ወደ ጌታ
ከመጣሽ፣ከወዲሁ እግዚአብሔር ልብሽን በደስታ ይሞላዋል፡፡የነፍስሽ ጉዳይ መፍትሔ ካገኘ ደግሞ፣ያ እንዴት እንደሚሆን መስማት ትፈልጊያለሽ
?” ብዬ ጠየቅኋት፡፡ “በእርግጥ፣እሺ…ፈቃደኛ ነኝ’’
ብላ መለሰችልኝ፡፡
ከዚያም ወንጌልን በሚገባት
መንገድ ተረኩላት፡፡በመስቀል ላይ የተሠራውን የክርስቶስን ገድልና ለሕይወቷ ያለውን ዕቅድ አብራራሁላት፡፡ “አሁን ፈቃደኛ ነሽ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝሽ ተቀበይዋለሽ፣ትከተይዋለሽ
እናም ምሕረቱንና የዘላለም ሕይወትን ትቀበያለሽ ?” ብዬ ጠየቅኋት፡፡እሷም “እቀበላለሁ፤የት እንደምሄድም አላውቅም፣ግራ ገብቶኛልና” ስትል መለሰችልኝ፡፡ከዚያም አብረን ጸለይን፡፡እኔም
በተከታታይ ያለማቋረጥ እየሄድኩ ለብዙ ጊዜ ጐበኘኋት፡፡ከነዚያ ጉብኝቶች ባንዱ እንዲህ አለችኝ፣ “ታውቃለህ ጆን ፣ባንድ በኩል ይህ አደጋ እንኳ ሆነ እላለሁ፤ባይሆን ኖር፣ጌታ
ኢየሱስን አላውቀውም ነበር፡፡” ይህ መረዳቷ ለኔ ትልቅ ደስታን ፈነጠቀልኝ፡፡እናም ለራሴ ደጋግሜ እንዲህ አልኩኝ፡-THIS MATTERS/ይህ ይበልጣል !!
ከዚህ መለኮታዊ ገጠመኝ በኋላ ሕይወቴ ሙሉ በሙሉ ተቀየረ፡፡አተያዬ 180 ዲግሬ ዞረ፡፡የዚች
ልጅ ለወንጌል ልቧን መክፈቷ፣ጌታ በዚህ ዙሪያ እንደሚፈልገኝም መረዳትን ሰጠኝ፡፡ልጅቷም የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ ሆነች፡፡ከዚያም
ተሳክቶላት፣ግሩም ከሆነ ክርስትያን ወንድም ጋር ተጋባች(ያው ችግሯ እንዳለ፣በዊልቼር እንዳለች)፡፡ታዲያ ወደ ኋላ ስመለከተው፣ከሷ
ጋር የነበረኝ ግንኙነት የወንጌሉን ጌታ ኢየሱስን እንዳገለግል ትልቅ ተጽዕኖን አሳድሮብኛል እላለሁ፡፡በወንጌል ኃይል በዚያ ዓይነት
ሁኔታ ከተጐበኘሁ በኋላ ፣እንዲህ ብዬ አሰብኩ፤-
“በቃ! ይህንን ነው
በሕይወቴ የምፈልገው፡፡ሌላ ነገር እንደዚህ በተቀራራቢ ተወዳዳሪነት እንኳ ሊመጣ አይችልም!!”
ጆን ማካርተር
No comments:
Post a Comment