Friday, October 24, 2014

ቴሪ ዊልሰንን የታደገው ድምፅ

ቴሪ ዊልሰንን የታደገው ድምፅ

በ2011 ዓመተ ምሕረት ከከባድ ኢንፌክሽን የተነሣ ሁለት ጊዜ “የሞት ጥላ” ውስጥ ወደቅሁ፡፡ሁለተኛው “የሞት ጥላ” ከመጀመሪያው የከፋ ነበርና፣ለሞት የቀረኝም የሰዓታት ጊዜ
ነበር፡፡ሆስፒታል ውስጥ ስደርስ የነበርሁበት ሁኔታ፣በነቃና ራሱን በሳተ ሰው መሃከል ነበር፡፡

ኢንፌክሽኑ በጣም ከባድ ስለሆነ ኩላሊቶቼ ሥራ አቁመው ነበር፡፡ልቤና ሳንባዬ ሕይወቴን የማስቀጠል ሥራ ላይ ተንጠልጥለው ነበር፡፡የሞትን ሽታ እያሸተትሁ ስለነበር ምንም የመትረፍ ተስፋ አልነበረኝም፡፡

ክርስትያን በመሆኔ በእግዚአብሔር ቃል አምናለሁ፡፡በዛ ጨለማ ውስጥ እያለሁ “በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም” (መዝሙር ዳዊት 23:4) የሚለው ቃል ወደ መንፈሴ ድንገት መጣና ቃሉን እያሰላሰልሁ መጸለይ ጀመርሁ፡፡ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለሆነ ክፉን አልፈራም” ብዬ ደጋግሜ አወጅሁ፡፡የሞትን ጥላ ፊት ለፊት በድፍረት እያየሁ “ሕይወቴ በጌታ እጅ ነው” አልሁት፡፡ከዚያም በጣም የሚገርም ነገር ተከሰተ፡፡በኃይል እንደፈራች ጥንቸል በሽታው ከእኔ እየሸሸ ሄደ፡፡ዶክተሮቹ እስኪገረሙ ድረስ በፍጥነት አገግሜ ካልጋዬ ተነሣሁ፡፡ከዛ ጊዜ ጀምር እስከ አሁን ድረስ በፍጹም ጤንነት ላይ
እገኛለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment