የውስጥ አካላቴ በምወስዳቸው
ኬሚካሎች የተበከለና የደነዘዘ ስለ ነበር፣ስሜት ማለት ምን እንደ ሆነ አላውቅም ነበር፡፡ዶፓሚን መቼ እንደምተኛ ይነግረኛል፡፡አልኮሆል
ወደ መኝታ መሄድ እንደሚገባኝ ያሳውቀኛል፡፡አደንዛዥ መድኃኒቶች መቼ እንደምሰርቅ፣መቼ እንደምዋሽ፣መቼ እንደማታልልና መቼ እንደምደባደብ
ይነግሩኛል፡፡እኔም በታማኝነት ለነዚህ የሱስ ቀንበሮች ታዛዥ ነበርሁ፡፡
ስሜ ሐውስተን ያሬድ ሲሆን፣በክርስትያን
ቤተሰብ ውስጥ ነው ያደግሁት፡፡ከአደንዛዥ ዕፅ፣አልኮሆልና ቁማር ባገኘሁት ማንነት የተነሣ፣የቤተሰቦቼን እምነት እርግፍ አድርጌ ተውሁኝ፡፡ሜት
የሚባል አደንዛዥ መድኃኒት እየሸጥሁ ብዙ ገንዘብ በቀላሉ አገኝ ነበር፡፡ለጊዜውም ቢሆን ኑሮዬን ወደድሁት፡፡ለ 12 ሰዓት ያህል
ብቻ ሳይሆን ከፈለግሁኝ ለ 3 ቀናት ሳላቋርጥ ቁማር መጫወትን ተክኜበት ነበር፡፡ማድረግ የነበረብኝ ነገር የምወስደውን የአደንዛዥ
መጠን ከፍ ማድረግ ብቻ ነበር፡፡ነገር ግን እየዋለ እያደር የምወስደው መድኃኒት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረኝ፡፡
ሜት በሚባለው አደንዛዥ ስሜ
ገነነ፡፡ዙሪያዬን በጓደኞችና በአደገኛ ቡድኖች ተከበብሁ፡፡ቢሆንም ፍርሃትና ጥርጣሬ በሕይወቴ ነገሡ፡፡ስለዚህም ሽጉጥ አይለየኝም
ነበር፡፡ፓሊስም ቅንጣት የማያስፈራኝ ሰው ነበርሁ፡፡ለኔ እስር ቤት መታሰር ቀልድ ነበር፡፡ቢሆንም የእስር ጊዜ እየጨመረ መሄዱ አሳሰበኝ፡፡አንድ
ጊዜ 3 ዓመት ተኩል ታስሬ ስፈታ፣ከወንድሜ ጋር መኖር ጀመርሁ፡፡ወንድሜም እንደኔው ሜት ይነግዳል፡፡አንድ ቀን በወጣበት ሳይመለስ
ቀረ፤ደብዛው ጠፋ፡፡ከዚያም ከሜት ጋር በተያያዘ አደገኛ ወንጀል መኪና ሰርቄ ስሸሽ፣ፓሊሶች በመኪና አሳድደው ያዙኝና 7 ዓመት አሰሩኝ፡፡በዚህ
ሰዓት ፍርድ ቤቱን ፍርዱን እንዲቀንስልኝ ተማጸንሁ፡፡ ነገር ግን ልመናዬ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ይህ ሁኔታ ልቤን በኃይል ሰበረው፣አዘንኩም፡፡ስለዚህም
ሕይወቴን መለወጥ አለብኝ ብዬም ወሰንሁ፡፡
በመጨረሻም እዚያች ጠባብ እስር
ቤት ውስጥ እግዚአብሔር በሚደንቅ ሁኔታ አገኘኝ፡፡ልክ ሰው እንደተናገረኝ ያህል “ወደ እኔ ተመለስ” የሚል የማያሻማና የማያጠራጥር
ድምጽ ሰማሁ፡፡ከሰማሁት ድምጽ የተነሣ፣ሕይወቴ በፍጥነት ተለወጠ፡፡ሰላምና ደስታ አጥለቀለቀኝ፡፡ጌታ እንደ ማረኝ ታወቀኝ፡፡ተሸክሜው
የነበረው የሱስ ቀንበር ተነነ፡፡ሁለት ሺህ ፓውንድ የሚመዝን ዝሆን ከላዬ እንደ ተነሣ ያህል ነበር የተሰማኝ፡፡
ከዚያም መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናትና
መጸለዬን ተያያዝኩት፡፡የእግዚአብሔር ፍቅር በሕይወቴ ውስጥ የነበረውን ባዶነት ሞላው፡፡በአደንዛዣ ዕፅ የማገኘው ሰላምና መረጋጋት
ጊዜያዊና ቶሎ የሚበን ነበር፤አሁን ግን ዘለቄታ ያለው ሰላምና ደስታ አለኝ፡፡ከዚያም ጌታ ትልቅ ተዓምር አደረገልኝ፡፡እንዲህ ነበር
የሆነው፡፡ዘጠኝ ወር ከታሰርሁ በኋላ ከማረሚያ ቤቱ ውጪ የጸባይ ማረሚያ ፕሮግራም ወይም ኮርስ እንድወስድ ተደረግሁ፡፡ያ ፕሮግራም
ለወደፊቱ አኗኗሬ ዓይኔን ከፍቶልኝ ተጠናቀቀ፡፡በዚህ ሰዓት የወጣቶች ፓስተር በመሆን አገለግላለሁ፡፡ጌታ ላና የምትባል ጌታን የምትወድና
የተባረከች ሚስት ሰጥቶኛል፡፡ሕይወቴ ወደ ኋላ ላይመለስ ተለውጧል፡፡
በዚህ ሰዓት ከማንኛውም ሱስ
ነፃ ነኝ፡፡የአልኮሆል ባሪያ አይደለሁም፡፡ወንጀለኛ አይደለሁም፡፡አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡፡አሁን በጌታ ጸጋ አዲስ ሕይወት
አግኝቼና ታድሼ ግሩም ሕይወት እየመራሁ እገኛለሁ፡፡ስሙ ለዘላለም ይባረክ !
No comments:
Post a Comment