ስሜ ሪኪ ክሪስማስ ይባላል፡፡ከጓደኞቼ ጋር ክፍት
የሆነ ጋራጅ ወይንም መኪና ካገኘን ዘርፈን መሄዱን ተክነንበታል፡፡በውስጤ “ማንም ሰው ሊያቆመኝ አይችልም” የሚል የራስ ትምክህት
ነበረኝ፡፡እንዳውም “እግዚአብሔር ራሱ ሊያቆመኝ አይችልም” ብዬም አስቤ አውቃለሁ፡፡
በማኅበረሰቡ ውስጥ አደገኛ ጠንቅና አሸባሪ መሆን
የጀመርሁት ጉርምስና እንደ ጀማመረኝ ነው፡፡በሕይወቴ አንድ ግብ ብቻ
ነበረኝ፡፡እሱም “እዚህ ምድር እስካለሁ ድረስ፣እደሰታለሁ፤ከዚያም ሲያበቃ ያበቃል” የሚል
ነበር፡፡
በእናት ብቻ ነው ያደግሁት፡፡እናቴ ገና ከሕጻንነቴ ጀምሮ “የባሕርይ ችግር” እንደ
ነበረኝ ትናገር ነበር፤ “እያደገ የሄደ የንዴት ችግር አለው” ትል ነበር፡፡ለሚቀርቧት “ዓመፀኛ ነው” ብላ ደጋግማ ስትናገር ሰምቻለሁ፡፡ቢሆንም
እግዚአብሔር እንደሚወደኝና ከኔ ጋር እንደ ሆነ እየነገረችኝ፣ቤተ ክርስትያን እንድሄድ ከመጣር ችላ ብላ አታውቅም፡፡
አንዱ ክፍል እኔ እግዚአብሔርን ይወድ ነበር፡፡ሌላኛው እኔ ደግሞ ከቤተ ክርስትያን
ውጪ ያለውን ሕይወት ማየት ፈለገ፡፡በቤተ ክርስትያን አያቸው የነበሩ ብዙዎቹ ድሆች ስለ ነበሩ፣ያንን ከባቢ ጠላሁት፡፡ስለዚህም ለጊዜውም
ቢሆን ከአካባቢው መራቅን መረጥሁ፡፡እውነተኛ ሕይወት ይገኝበታል ብዬ ያሰብኩትን ሁሉ እስከ ጥግ ድረስ አደረግሁ፡፡
በእንደዚህ ዓይነት ፍለጋ እያለሁ ነበር የታወቀ የወንበዴ(gang) ቡድን የተቀላቀልኩት፡፡እጅግ
አደገኛ ጊዜ ላይ ነበርና የነበርሁት፣”ፓሊስን መግደል ምንም ችግር የለውም፣ምንም አይደል ሰው ከ10 ሴቶች ጋር ቢተኛ፤አደንዛዥ
ዕፅ መሸጥ ምንም አይደል፤ምክንያቱም መኖር አለብህ፣መብላት አለብህ” ከሚሉ ለጋ ወጣቶች ጋር ነበር የተዋሃድኩት፡፡
ከእነዚህ ባልደረቦች ጋር ወደ አደገኛ ስርቆት ውስጥ ገባን፡፡የመኪና ውስጥ ቴፓችን
መስረቅ ነበር የኔ ኀላፊነትና ድርሻ፡፡ሌብነቱ አድጐ፣ቤት ሰብረን እየገባን መዝረፉ ተጧጧፈ፡፡ብዙ ገንዘብ ስለምናገኝ፣ልባችን እስኪጠፋ
እንዝናና ነበር፡፡ነፍሴ ከልጆቹ ነፍስ ጋር በፍቅር ተሳሰረች፡፡ከዚያም የተነሣ ወጣ ገባ እያልኩ የምማረው ትምህርት እስከ መጨረሻው
ተቋረጠ፡፡ለአካባቢው እጅግ አደገኛ በመሆኔ አካባቢው ተሸበረ፡፡በዚህ ሁሉ ግን እናቴ ተስፋ አልቆረጠችም ነበርና፣አብዝታ ትጸልይልኝ
ነበር፡፡ “እግዚአብሔር ምንም ሳይሆን ወደ ራሱ ይመልሰዋል” ብላ ታምንና በቅርቧ ላሉ ሰዎች ትናገር እንደ ነበረ ያካባቢው ሰዎች
መስክረውኛል፡፡
ጊዜው እየገፋ ሲሄድ፣የእናቴ ጸሎት ያልሠራ እስኪመስል ድረስ፣ነገሮች እየባሱ መጡ፡፡አንድ
ቀን የቅርብ ጓደኛዬ ተይዞ ወኅኒ ወረደ፡፡እዚያው እስር ቤት እያለ ወዲያው ይሞታል፡፡ከዚህ ወንድም ጋር እድሜያችን ተቀራራቢ ነበር፡፡የሚገርመው
ሕፃን ልጅ ነበረችው፡፡የሚቀበርበት ሳጥን ወስጥ በድኑ ተዘጋጅቶ ሳለ፣ሕፃኗ
ወደ ሳጥኑ እያየች እሪታዋን አቀለጠችው፡፡ያንን ትዕይንት እያየሁ “እንዲህ ነው የሚያልቀው/that is how it
ends” ብዬ ከልቤ ጋር አወራሁ፡፡ያ ልቤ ከልቤ ጋር የነበረው ንግግር የመንፈስ ቅዱስ ድምፅም እንደ ነበረ ምንም አልጠራጠርም፡፡ታዲያ
ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ቀጥሎም በዛ ሳጥን ውስጥ ራሴን አየሁት፡፡እጅግ ደነግጬ ነበርና፣ ከዚያ ቀን በኋላ ከጓደኞቼ ራሴን አርቄ
የጌታን ፊት መፈለግ ጀመርሁ፡፡እውነተኛ ንስሐ ገባሁ፡፡ጌታን ማረኝ ብዬ አምርሬ ተማጸንሁት፡፡ከዚየ በኋላ ያንን የወንበዴ ቡድን
በኪሎ ሜትር ተለየሁኝ፡፡
ወዲያው በጌታ ምሕረት ሥራ አግኝቼ መሥራት ጀመርሁ፡፡ቤተ ክርስትያን መሄድ አዘወተርሁና፣ውስጤ
በሚገርም ሁኔታ ታደሰ፡፡ያለ ጌታ ሕይወቴ ድምጥማጡ እንደሚጠፋ በሚገባ ገባኝ፡፡ከጊዜያዊ ደስታ ይልቅ፣ከሱ ጋር መሆን እንደሚሻል
አስተዋልሁ፡፡ከቤቱ ላልወጣም ወሰንሁ፡፡በዚህም ምክንያት ልቤ በጥሩ ሁኔታ ተረጋጋ፡፡
እናቴ መቼም ቢሆን ገፍታኝና ትታኝ አታውቅም፡፡ይህን ባሰብኩት ቁጥር ይገርመኛል፡፡አሁንማ
ግንኙነታችን እጅግ ታድሷል፡፡ይሄ ለኔ ብቻውን ትልቅ በረከቴ ነው፡፡አዘውትረን አብረን እንጸልያለን፣እናሳልፋለንም፡፡በዚህ ሰዓት
ባል፣አባትና ፓስተር ሆኛለሁ፡፡ሌሎችን እንደ እኔ ከመሰለ ክፉ መንገድ እንዲመለሱ እረዳለሁ፡፡በጥቅሉ ጌታ ሕይወቴን ልናገረው ከምችለው
በላይ በሁሉም መስክ ባርኮታልና ስሙ የተባረከ ይሁን!
No comments:
Post a Comment