የሀጢያት
ስርና መፍትሄው
ሀጢያት ውስጣችን ያለና
የሚኖር መርዝ ነው፡፡እንደዚያም ሆነን ነው የተፈጠርነው(መዝ
51፡5)፡፡ልክ
እንደ ማግኔት
ህግ ሁለንተናችንን
ወደ ክፋት
በማዘንበል ከእግዚአብሔር እንድናፈነግጥ
ይስበዋል፡፡እንግሊዝኛው ‹‹indwelling sin›› ብሎ ነው የሚገልጸው-አብሮን
ነዋሪነቱን ለመግለጽ፡፡ለዚህ ነው
በጎን ከማድረግ
ይልቅ ክፋትን
ማድረግ የሚቀለን፡፡
እግዚአብሔር በምህረቱ አስቦን
ካልሳበን በስተቀር በውስጣችን
እግዚአብሔርን የሚፈልግ ነገር
የለንም(ሮሜ 3፡11)፡፡ቃሉ እንዲህ
ይነበባል፡-
‹‹ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤አስተዋይ የለም፤እግዚአብሔርን የሚፈልግ
የለም፤ሁሉም ተሳስተዋል በአንድነት
የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ቸርነት የሚያደርግ
የለም አንድ
ስንኳ የለም››
ይህ ነው
ትክክለኛ ማንነታችን፡፡ውጫችን ሀይማኖተኛ
ቢመስልም፤ውጫችን የሞራል ሰው
ቢመስልም እግዚአብሔር በቸርነቱ
ካልጠራን እና ካላወጣን በስተቀር ከዚህ
ማጥ የመውጣት
አቅሙም ሆነ ዝንባሌውም የለንም(ዮሀ
6፡44)፡፡አንድ
የእግዚአብሔር ሰው ‹‹በግብዣ ብቻ ወደ እርሱ እንድንመጣ ብንጋበዝ ሁላችንም
እንጠፋ ነበር›› ብለዋል፡፡በእዝራ 1፡1-3 እና ቁጥር 5 ላይ ‹‹የህዝቡን መንፈስ
አነሳሳ››እንደሚል ‹‹መፈለግንም
ማድረግንም በእኛ ውስጥ የሚሰራው››(ፊሊ
2፡13) እራሱ
ነው፡፡የተወደደችው ሰአት ስትመጣ ልባችን ለጥሪው
ያነሳሳል፡፡ይህም የሚያሳየን ሰው
ወደ ጌታ
ለመምጣት ያለበትን የተጋረጠ
የውስጥ አደጋ ነው፡፡ምህረቱ ብዙ ነው እንጂ ብዙዎቻችን የት ነበርን? ይህ በሚገባ
ሲገባን በሀይል አመስጋኞች
እንሆናለን፡፡
ሀጢያት ብዙ ውጤቶች አሉት፡፡መዝ 38 ስታጠኑ
በእያንዳንዱ ጥቅስ ላይ የተዘረዘሩትን ትኩረት
ሰጥታችሁ ብታይዋቸው ያሉብንን
አደጋዎች በሚገባ መገንዘብ
ትችላላችሁ፡፡መዝ 38፡3-10 ላይ ብዙዎቹ የሀጢያት
መዘዞች ተጠቅሰዋል፡፡ዳዊት በዚህ
ክፍል ውስጥ፡-
- ለአጥንቶቼ ሰላም የላቸውም ይለናል
- ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም በማለት የውስጥ መንፈሳዊ ሁኔታውን ይነግረናል
- ጎሰቆልሁ ተዋረድሁም በማለት የሀጢያትን የማሸማቀቅና የመከራ መዘዝ ያሳየናል
- በማህበራዊ ህይወቱ ስድብን እንደጠገበ ይነግረናል
- ጤና እንደሌለውም ይገልጽልናል
- በድንጋጤ ውስጥ እንዳለ ይነግረናል
- ሀይል እንዳልቀረለት ገልጾልናል
- ማየት እንደተሳነውም ሁሉ ጽፎልናል
- ከነዚህም የተነሳ ማህበራዊ ህይወቱ እንደተበላሸ እና ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንደራቀው እናያለን
የዚህን መዝሙር ሙሉ ምእራፍ ስናነብ የምንገነዘበው ሀጢያትንና የሚያመጣውን መዘዝ ነው፡፡ማለትም ሀጢያት ፡-
- ነፍስን ያደክማል
- ሀይልን ያሳጣል
- ስብራትን ወደ ህይወታችን ያመጣል
- መንፈሳዊ እይታችንን ይጋርዳል(መዝ 40፡12)
- ማህበራዊ ህይወታችንን ያበላሻል
ሰው በተፈጥሮው የሀጢያት ባሪያ ነው(ዮሐ 8፡36)፡፡ለዚህ ነው ዳግመኛ መወለድ የሚያስፈልገን(ዮሀ 3፡3-8)፡፡ለዚህ ነው የልብ መገረዝ የሚያስፈልገን(ቆላ 2፡11-13፡፡ለዚህ ነው ሀዋርያው ዮሐንስ በዮሐ 3፡9 ላይ ‹‹ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ሀጢያትን አያደርግም ዘሩ በእርሱ ይኖራልና ከእግዚአብሔር ተወልዶአልና ሀጢያትን ሊያደርግ አይችልም››ብሎ የሚነግረን፡፡ስለዚህ ነው ዳግመኛ ስንወለድ ድንገት ተሳስተን እንጂ ወድደን፣ተስማምተን እና ደስ ብሎን ያለምንም ወቀሳ ሀጢያትን መስራት የምናቆመው፡፡ትልቅ ለውጥ በህይወታችን ስለሚኖር እርሱን ደስ ለማሰኘትም እንቀናለን፡፡
ኤፌ 2፡1-2 ዳግመኛ ከመወለዳችን በፊት የነበርንበት መንፈሳዊ ሀኔታ ነው የሚያሳየን፡፡እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹በበደላችሁና በሀጢያታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤በእነርሱም በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ በፊት ተመላለሳችሁባቸው፡፡በእነዚህ ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ የስጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን በስጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበር እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን››
አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ እንደነበርን አገላለጹ በሚገባ ያሳየናል፡፡የስጋችንንና የልቡናችን ፈቃድ ነበር መሪያችን፤አለቃችንም በአየር ላይ የሚሰራው የመንፈስ አለቃ፡፡ከዚህ አይነት ዘግናኝ ሁኔታ ነው መንጭቆ የሚያወጣን በትህትና እጅ ወደ ላይ ብንል፡፡
ለዚህም ነው በዋነኛነት ኢየሱስ ወደዚች ምድር የመጣልን፡፡ኢሳ 42፡6-7 ላይ የኢየሱስን ተልእኮ ሲናገር እንዲህ ይላል፡-
‹‹እኔ
እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼህማለሁ፤የእውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለህዝብ ቃል ኪዳን ለአህዛብ ብርሀን አድርጌ እሰጥሀለሁ››
ወደ ጌታ ያልመጣ ሰው የሀጢያት ወህኒ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ቃል የሚነግረን፡፡እውሮችም ጭምር እንደሆንንም ይነግረናል፡፡ከእርሱ ጋር ተስማምተን ‹‹እነሆኝ›› ብለን እራሳችን ለዚህ የህይወት ብርሀን ስንሰጥ ከሀይለኛ የግዞት ሰፈር እንወጣለን፡፡አይኖቻችንም ተከፍተው የት እንደነበርን እናስተውላለን፡፡የነጻነት አየር እንተነፍሳለን፡፡ከወቀሳ እና ከእፍረት እንድናለን፡፡ማህበራዊ ግንኙነታችን ይታደሳል፡፡መለኮታዊ ሰላምና ደስታን ምን እንደሚመስል መቅመስ እንጀምራለን፡፡
ተግተን ከቀጠልንም እየተለቀቀን እና ወደ ሰፊ ስፍራ እየወጣንና(መዝ18፡19) እየተለወጥን እንመጣለን፡፡ዳዊት ከእንደዚህ አይነት ድል በኋላ መዝ 30፡11 ላይ ‹‹ክብሬ ትዘምርልህ ዘንድ ዝምም እንዳትል ልቅሶዬን ለደስታ ለወጥህልኝ፤ማቄን ቀድደህ ደስታን አስታጠቅኸኝ››ብሎ እንደሚናገር ሀዘናችን እና ቁዘማችን ሁሉ በሰላምና
በደስታ ይቀየራል፡፡ይህን በህይወቴ ስላየሁ ህያው ምስክር ነኝና ሳታቅማሙ በፊቱ በትህትና ኑና ውደቁ ይገላግላችኋል፤በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነጻነትን ያጎናጽፋችኋል!!
Bekele
Belachew

beke_abay@yahoo.com
No comments:
Post a Comment